@mesertatihawusteadbarekidusan
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፦ በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች እና መንፈሳዊ ትምሕርቶችን ያገኙበታል። ዘማሪ ዲያቆን ፍጹም ከበደ
5470 members. 20 publications at this channel.
እንግዳው በጭቅጭቃቸው የታወቁ ባልና ሚስት ነበሩ መሽቶ በነጋ
🕯🕯እንግዳው🕯🕯
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈

በጭቅጭቃቸው የታወቁ ባልና ሚስት ነበሩ። መሽቶ በነጋ ቁጥር ውሏቸውን የሚያሟሹት በጭቅጭቅ ነው። ከዕለታት አንድ ቀን እንግዳ ወደ ቤታቸው ዘለቀ። በአገሩ ልማድ መሰረት እግር አጥበው፣ ቀለብ ሰፍረው፣ ምንጣፍ ለቀው ካስተናገዱ በኋላ የመኝታ ሰዓት እስኪደርስ በጎጆዋ መካል ከተለቀቀው ምድጃ ላይ የሚቀጣጠለውን እሳት እየሞቁና የሚዘገን ጥሬ እየቆረጠሙ ወግ ይዘዋል ።

በይኽ መሃል የለመደው የባልና የሚስቱ መቋጫ የሌለው ጭቅጭቅ ተጀመረ። እስከአሁን የዘገየውም ስለ እንግዳው ክብር ነበር። ልማደኞቹ በቃላት ጦርነቱ አንተ አንቺ ሲባባሉ ቆዩና ባልየው አጠገቡ የተቀመጠውን እንግዳ ከምንም ባለመቁጠር ሚስቱን ሊመታት አስቦ ምድጃው ከጉረሳቸው የፋሙ እንጨቶች መሃል አንዱን መዘዝ አደረገና ተነሳ።

ሚስትም የዋዛ አልነበረችምና ሌላኛውን የፋመ እንጨት መዘዘችና "እስኪ ወንድ ነህ...." በማለት ከፊቱ ቆመች የባልና ሚስቱን ሁኔታ ሲታዘብ የቆየውም እንግዳም ከምድጃው አንድ የፋመ እንጨት መዘዝ አድርጎ ቆመ።

ነገሩ ያላመረው አቶ ባል ወደ እንግዳው ዞር ብሎ "እኔ ሚስቴን ልመታ ነው እሷም እኔን ልትመታ ነው አንተ ደግሞ ማንን ልትመታ ነው የፋመውን እንጨት ያነሳኸው?" ብሎ ቢጠይቀው እንግዳውም " አ.....አይ ጌታው የቤቱ ሥርዓት መስሎኝ ነው" አለ ይባላል።

❤️❤️🎈❤️❤️🎈❤️🎈❤️🎈❤️🎈🎈

ብዙዎቻችን በክርስትናችን ስንቀልድ አይታወቀንም ብዙ ተመልካችም እንዳለን ስለማናውቅም ግራና ቀኙን ሳናይ እንጨቃጨቃለን፣ እንጣላለን ለክርስቲያናዊ ሥነ ምግባራችን አንጠነቀቀም ታድያ በእኛ ምክንያት ብዙዎች ይሰነካከላሉ።

ሰውየው የቤቱ ሥርዓት መስሎኝ ነው እንዳለው እንግዳ መጠጥ ፣ ሲጋራ ማጨስ ጫት መቃም በኢትዮጲያ ቤተክርስቲያን እንደሚፈቀድ አርገው ያስባሉ።
ማስተዋል ያብዛልን!
👇👇👇👇👇👇
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
ሰበር ዜና አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ሰበር መረጃ
Forwarded from ETS Support
ሰበር ዜና ‼️

አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ሰበር መረጃ እየወጡ ነው ቶሎ ከታች ያለውን link በመጫን አጋር ቻናላችንን ይቀላቀሉ ቶሎ በሉ🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

https://t.me/joinchat/S3mdkjaTo5RkNWE0
ክርስታያን ከሆኑ ወደነዚህ ቻናል ገብተው subscribe ያድርጉ በዚህ
ሰላም ሰላም ሰላም በያላችሁበት ውድ የየኔታ ወንበር ተማሪዎች
ሰላም ሰላም ሰላም በያላችሁበት ውድ የየኔታ ወንበር ተማሪዎች እንዴት ናችሁ ? በቅርብ ቀን ዛሬ ምሽት ወይ ነገ መልክዓ ዮሐንስ መጥምቅ ወይም መልክዓ ኪዳነ ምሕረት በዜማ እለቃለሁ።

ምርጫችሁን አሁኑኑ አሳውቁኝ። የትኛው ይቅደም ? መልሳችሁን @Zerea_Buruk13 ላይ አስቀምጡልኝ።
Watch በሚያስፈራው ግርማ ድንቅ ዝማሬ በዘማሪ ግዛቸው ሹካ
Forwarded from ናታኒም TUBE (ማኔቴቄል ፋሬስ)
Watch "በሚያስፈራው ግርማ ድንቅ ዝማሬ" በዘማሪ ግዛቸው ሹካ ግጥምና ዜማ ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ subscribe ሼር በማድረግ አዲስ የምንለቃቸው ዝማሬ ይጋበዙ !" on YouTube
https://youtu.be/WO6XhrjcsJI
ፆም ገንዘብ ያደረጉትን መንፈሳዊ ስራ ያሰራቸዋል ማር ይስሐቅ
"ፆም ገንዘብ ያደረጉትን መንፈሳዊ ስራ ያሰራቸዋል" /ማር ይስሐቅ/

የበረከት ፆም ያድርግልን !


@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan

#ወሰንየለው
የኤልያስ መሶበ ወርቅ አንቺ ነሽ መሶበ ወርቅ እንተ
#የኤልያስ_መሶበ_ወርቅ_አንቺ_ነሽ
"መሶበ ወርቅ እንተ ኤልያስ"

ኤልያስ ከንግሥቲቱ ኤልዛቤል ሸሽቶ በመንገድ ሳለ ድካም ቢያስቸግረው ከአንዲት ዕጽ ሥር አረፍ አለ። እንቅልፍም ወስዶት ነበር። በዚህ ወቅት የእግዚአብሔር መልአክ ቀስቅሶት ቢነሳ ከራስጌው እንጀራ ባገልግል ውሀ ደግሞ በመንቅል ተዘጋጅቶ አገኘ ያን ተመግቦ ተመልሶ ተኛ። ዳግመኛ ቀስቀሰው በልቶ ተኛ። ለሶስተኛ ጊዜም መንገድህ ሩቅ ነውና እስክትጠግብ ድረስ ተመግብ አለው እርሱም ያንን ተመግቦ ዓርባ ሌሊት እና ዓርባ ቀን ሙሉ ያለድካም ተጉዞ አርጓል። ይህ ሁሉ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነው። ኤልያስ የምእመናን ምሳሌ÷መሶብ የእመቤታችን÷ወርቅ የንጽህናዋ÷ኅብስት የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ነው።

ኤልያስ ብርታት አግኝቶ አርባ ቀን የተጓዘው ከመሶብ በተገኘው ኅብስት ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የዘላለም ሕይወት የሚያስገኘውን እና አማናዊውን ኅብስት ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ ጥንካሬ ይሆነን ዘንድ እውነተኛ መብልዕ የሰጠንን ክርስቶስን አስገኝታለች። ይህ ምሥጢር ግሩም ነው። ለዓለም ሁሉ የሚሆን የተራበች ነፍስን የሚያጠግብ ክርስቶስ መሶበ ወርቅ በተሰኘች በእመቤታችን አደረ። በመሶብ ለሰው ልጅ ብርታት የሚሆን እንጀራ እንደሚገኝ በእርሷም የነፍስና የሥጋ ሕይወት የሆነ ክርስቶስ ተገኝቷል። ዓለምን የሚያጠግብ አምላክ በእርሷ ታየ። ንጽህት ሆና የተገኘች እመቤታችን ህብስተ ሕይወት ክርስቶስን በድንግልና ጸንሳ ወለደች። ስለዚህም ድንቅ ሥራ እናመሰግናታለን የሕይወት ምግብን አስገኝታልናለችን እለት እለት እናወድሳታለን። ድንግል ሆይ የተራበች ሰውነታችንን በኃጢአት የጠወለገች ነፍሳችንን የሚያድስ እውነተኛ መብልዕ ክርስቶስን የወለድሽ ነሽና በብዙ እናመሰግንሻለን።

ዲ/ን ሞገስ አብረሃም

@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan

#ወሰንየለው ባሕሩ
ከጾም የሚገኘው ጥቅም ብዙ ሰዎች አንዳቸው ለሌላቸው 39
ከጾም የሚገኘው ጥቅም...
©

"ብዙ ሰዎች አንዳቸው ለሌላቸው 'የጾሙ ግማሽ አለፈ፣ ግማሹን ጾም ፈጽመናል' ሲባባሉ እመለከታለሁ። እኔ ግን እንዲህ ያሉት ሰዎች የጾሙ ግማሽ በማለቁ በዚህ እንዳይደሰቱ እመክራቸዋለሁ። ከዚህ ይልቅ በጾማቸው የኃጢአታቸው ግማሽ ተወግዶ ስለ መሆኑ እንዲያስቡና በእርግጥ በጾማቸው እንደዚህ ዓይነት ጥቅም አግኝተው ከሆነ ያን ጊዜ ቢደሰቱ መልካም ይሆናል። ልናስብበት የሚገባው ነገር ይህ ነውና፤ ጾሙን ስንጨርስ ልክ ስንጀምር እንደ ነበርነው ዓይነት ሰዎች ሆነን ሳይሆን ከኃጢአታችን የነጻን ሰዎች ሆነን እንድንጨርሰው መሆንን ነው። ...የክረምት ጠቀሜታው የበለጠ የሚታወቀው ወቅቱ ካለፈ በኋላ ነውና። ያን ጊዜ የአበባዎች ማበብ፣ የአዝመራው ማፍራት፣ የዛፎች መለምለም፣ እነዚህ ሁሉ በመታየታቸውና በመውጣታቸው ከክረምቱ ያገኙትን ጠቀሜታ በግልጽ ይናገራሉ። በእኛም እንዲሁ ይሁን። በጾም ወራት ያገኘነው መንፈሳዊ ጥቅም ጾሙ ካለፈ በኋላ በእኛ ላይ በሚያፈራው መልካም ፍሬ ጠቀሜታው ግልጽ ሆኖ እንዲታይ ይሁን። እንዲህ ካደረግን ጾሙ እንደገና ተመልሶ ሲመጣ በደስታ እንቀበለዋለን። ...ከጾም የሚገኘውን ጥቅም በትክክል የተረዳነውና በጾማችን ወቅት ያንን ጠቀሜታ የምንቀምሰው ሆነን ቢሆን ኖሮ ጾሙ በየቀኑ እንዲመጣ በተመኘን ነበር። እንዲህ ሆኖም የጾሙን መምጣት መናፈቃችንንና ለጾም ያለንን ጉጉትና ናፍቆት መቀነስ የለብንም፣ እርሱን በማሰብ መፍራትና መጨነቅም አይኖርብንም።"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት 18፣ ቁ. 1-2)


@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan


#ወሰንየለው ባሕሩ
በሚያስፈራው ግርማ በቅርብ ቀን በናታኒም ቲዩብ በዘማሪ ግዛቸው
በሚያስፈራው ግርማ በቅርብ ቀን በናታኒም ቲዩብ በዘማሪ ግዛቸው ሹካ ግጥምና ዜማ ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ subscribe Sher በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/No-mmpKMgN0
https://youtu.be/No-mmpKMgN0
https://youtu.be/No-mmpKMgN0
ንግስተ አዜብ ስለ ጥበብ እንዲህ አለች ወገኖቼ ነገሬን
" ንግስተ አዜብ ስለ ጥበብ
እንዲህ አለች"!!!!


ወገኖቼ ነገሬን አድምጡኝ ፡፡ እኔ ጥበብን እሻለሁ ፡፡ ልቤም አውቀትን ትፈልጋለች በጥበብ ፋቅርም ተነድፌ አለው በጥበብ ገመዶች ተይዣለሁ ፡፡
" ጥበብ ከወርቅና ከብር መዛግብት ትሻላለች ፡፡ ጥበብ በምድር ከተፈጠሩት ሁሉ ትበልጣለች ፡፡ ጥበብን ከሰማይ በምን ይመስሏታል ፡፡ ከማር ትጣፋጣለች ፡፡ ከወይን ታስደስታለች ፡፡ ከፀሐይ ታበራለች ፡፡ ከጣፈጡ ምግቦች ታጠግባለች ፡፡ ከመቶ ሺ ወረቅና ብር ታከብራለች ፡፡ ለልብ አስደሳች ፣ለአይኖች መብራት ፣ ለእግር ቅልጥፋና፣ ለደረት ጥሩር ፣ለራስ አክሊል፣ ለአንገት የወርቅ ማርዳ፣ ለወገብ መታጠቂያ ፣ ለጆሮ ማዳመጫ ፣ ለልብ ብልሀት ፣ ለሙሁራን ትምሕርት ፣ለልበኞች መፅናኛ ለሚፈልጉ ክብርን ሰጪናት ☞ ☞ "መንግስት ያለ ጥበብ አይቆምም ፡፡ ሃብትም ያለጥበብ አይጠበቅም ፡፡ እግርም ያለጥበብ በቆመበት አይፀናም ፣ ልሳንም ያለጥበብ የተናገረው አይወደድም ፡፡ ጥበብ ከንብረት ሁሉ ትሻላለች ፡፡ ወርቅና ብር የሰበሰበ ያለ ጥበብ አይጠቅመውም ፡፡ ጥበብን የሰበሰብ ከልቡ ማንም አይቀማውም ፡፡ ☞☞ ሰነፎች የሰበሰቡትን ጠቢቦች ይበሉታል ፡፡ በበደለኞች ክፋት ቅኖች ይመሰገናሉ ፡፡ በሰነፎች ስህተት ጠቢቦች ይወደሳሉ ፡፡ ጥበብ ልዕልት ናት ፡፡
እንደ እናት እወዳታለሁ ፡፡ እሷም እንደ ህፃኗ ታቅፈኛለች ፡፡ እኔ ጥበብን ፋለጋ እከታተላለሁ ፡፡ እሷም እስከ ዘለአለም ትጠብቀኛለች ፡፡ እኔ ጥበብን እፈልጋታለሁ ፡፡ እሷም ለሁል ጊዜ ትሆነኛለች ፡፡ ዱካዋን እከታተላለሁ ፡፡ ከእሷም አልጣላም እጠጋታለሁ እሷም የድንጋይ ግንብ ትሆነኛለች ፡፡ ሃይልና ብርታትም ትሆነኛለች እደሰትባታለሁ ፡፡ ብዙ ሞገስም ትሆነኛለች የጥበብን ዱኳ ልንከተል ሸኮኖቻችንም በበሮቿ ደረጃ ሊቸነከር ይገባልና ፡፡ " እንፈልጋታለን እንገናኛታለን ፣ ከእኛም አትርቅም ፡፡ እናገኛታለን እንለምናታለን እንቀበላታለን ሁልጊዜ እንፈልጋት ፡፡ ልባችንን ወደ እርሷ እንመልስ ካሰቧት ታስባለች ፡፡ በሰነፎች ዘንድ ጥበብ አትታሰብም አያከብሯትም እናም አትወዳቸውም ፡፡ የጥበብ ክብር ጥበብን ማክበር ነው ፡፡ የጥበብ ፋቅር ጠቢብን ማፍቀር ነው ፡፡ ጠቢብን ውደደው ፡፡ ከእርሱም አትራቅ እሱን በማየት ጠቢብ ትሆናለህ ፡፡ እንደሱ ትሆን ዘንድ ከአፋ የሚወጣውን ሰማ ፡፡ እሱ በቆመበት ትቆም ዘንድ የእግሩን መጫሚያ እይ ፡፡ የጥበቡን ትርፋ ትቀበል ዘንድ ከእርሱ ፈቀቅ አትበል ፡፡ እኔም ሳላየው በመስማት ወደድኩት ፡፡ በእኔ ዘንድ የነገሩ የምስራች ውሃ ለተጠማ እንደሆነ በልቤ የተወደደ ሆኗል፡፡ መኳንቶቹ ወንዶቹና ሴቶቹ ባሪያዎችምና አማካሪዎችም☞☞ " እመቤታችን
ጥበብ እኮ ካንቺ አልታጣም ጥበብን ምትወጂ በጥበብሽ ነው ፡፡ እኛ ግን አንቺ ብትሄጂ ከአንቺ ጋር እንሄዳለን ፡፡ ብትቀመጪ ከአንቺ ጋር እንቀመጣለን ፡፡ ሞታችን ከሞትሽ ደህንነታችን ከደህንነትሽ ጋር ይሁን ሲሉ መለሱ ፡፡@ ዘ/ዲ ፋፁም ከበደ @

@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan
ክርስታያን ከሆኑ ወደነዚህ ቻናል ገብተው subscribe ያድርጉ በዚህ
እራሔል አዲስ ዝማሬ በናታኒም ቲዩብ በቅርብ ቀን ሰብስክራይብ
Forwarded from ElroyPromotionBot
እራሔል አዲስ ዝማሬ በናታኒም ቲዩብ በቅርብ ቀን! ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይውኑ
👇👇👇👇
https://youtu.be/KH1kUhCUVpg
https://youtu.be/KH1kUhCUVpg
https://youtu.be/KH1kUhCUVpg
ክርስታያን ከሆኑ ወደነዚህ ቻናል ገብተው subscribe ያድርጉ በዚህ
እራሔል አዲስ ዝማሬ በናታኒም ቲዩብ በቅርብ ቀን ሰብስክራይብ
እራሔል አዲስ ዝማሬ በናታኒም ቲዩብ በቅርብ ቀን! ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይውኑ
👇👇👇👇
https://youtu.be/KH1kUhCUVpg
https://youtu.be/KH1kUhCUVpg
https://youtu.be/KH1kUhCUVpg
ክርስታያን ከሆኑ ወደነዚህ ቻናል ገብተው subscribe ያድርጉ በዚህ
ከፍቅር የሚበልጥ ምን ነገር አለ ባልና ሚስት በሚኖሩበት
#ከፍቅር_የሚበልጥ_ምን_ነገር_አለ

ባልና ሚስት በሚኖሩበት አንድ ቤት ውስጥ ከመሸ በራቸው ይንኳኳል። ሚስት ለመክፈት ትሄዳለች ከዛም ባየችው ነገር በጣም ትገረማለች። 3 ነጫጭ ሽበት ያለባቸው የሚያማምሩ ባለግርማ ሞገስ ሽማግሌዎች ነበሩ። አቤት ግቡ ምን ፈልጋቹ ነው አለቻቸው ።ሦስታችንም አንገባም አንዳችን ነን የምንገባው ራሳችን እናስተዋውቅሽ አሉና ራሳቸውን ማስተዋወቅ ጀመሩ ።

1ኛው #ስኬት😇 እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባሁ አሳብሽ ሁሉ ይሳካል አላት።
2ተኛው #ገንዘብ💰 እባላለው እኔ ቤትሽ ከገባሁ ችግር የሚባል አይኖርም አላት።
3ተኛው #ፍቅር❤️ እባላለው ፍቅር ማብራሪያ የለውም አላት።

ከዛ ሚስት ባለቤቷን ላማማከር ብላ ወደ ውስጥ ገባችና ለባለቤቷ ነገረችው በነገሩ ተደንቆ እንዲህ አለ፦ በዕውነቱ ይሄ ዕድል ሊያመልጠን አይገባም ፤ ገንዘብን የሚያክል ነገር ደጅ ቆሞ መወያየት ግፍ ነው። ሰርቼ ከሰው በታች የሆንኩት ገንዘብ ሰለሌለኝ ነውና ፈጠን በይ ገንዘብን ወደቤታችን እንዲገባ ንገሪው አላት ባለቤቱም በሀሳቡ ተስማምታ ገንዘብን ልትጠራው ስትል ልጇ እንዲህ አላት፦ እማዬ ገንዘብ ገብቶ አባዬ እንደለመደው ማታ ማታ ከሚደበድብሽ ፍቅር ገብቶ ሰላምሽን ብታገኚ አይሻልም? አላት። እሷም በልጇ ሀሳብ ተደስታ ባልየውን ፍቅር ካልገባ ብላ ሞገተችው በመጨረሻም ፍቅር እንዲገባ ወስነው ወደ ሽማግሌዎቹ ሄዱና ፍቅር የተባልከው ሰው ወደቤታችን ግባ ይሉታል። እሱም ተከትሏቸው ገባ። ባልና ሚስቱም ዞር ብለው ሲያዩ 3ቱም ሰዎች ቤት ገብተው ቆመዋል ባልየው ደንግጦ እኛ በቤታችን እንዲገባ ያልነው ፍቅርን እኮ ነው አለ ። ከሽማግሌዎቹም አንዱ ዞር አለና ልክ ብለሀል ነገር ግን ፍቅር ካለ ስኬት አለ ፍቅር ካለ ገንዘብ አለ ። በማለት 3ቱም ወደቤታቸው ገቡ።

@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan
@MesertatihaWusteAdbareKidusan
ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች ግለ አውናን